Saturday, April 13, 2013

ሌጋሲው መማር መማር ብቻ



መሪ ማለት መምህር መምህር ማለት መሪ
እንዲህ ነው ሀሳቤ!!!!!


 መማር መማር ብቻ

እኛ እጣን ሳለን ገና ካልጋ ሳንወርድ
እዚያለው መምህር ነበር የሚያስፈራ ነበረ የሚያርድ
እነሱ ግን መጥተው
በፍፁም መምህር አትሆንም ብለው
ማቅለሚ ብዕሩን
መግረፊያ አርጩሜውን
ፊደል ገበታውን
ሁሉ ተቀብለው
ማስተማር ጀመሩ አዲስ ካርታ ስለው::
እኛም የነሱ ተማሪ
                                 እነሱ አስተማሪ       
እኛ ተመካሪ
እነሱ ዘካሪ
ሲሉን ሀ ብለን
ሲሉን ቀጥለን
የነሱን ትምህርት እፀፅ የሌለውን
እድገት የበዛውን
ተማርን ተማርን ይ¤ው ለዘመናት ፊደሉን ቆጠርን:::
እነሱ ……..መምህር ሳይቀይሩ
እኛኑ ሲመክሩ
ለእኛ ሲታትሩ
ለእኛው ሲዳክሩ
እኒሁ መምህር ሲኖሩ ሲኖሩ
እሱ አሳረፋቸው ……ደሞ ሌላኛውም
በእኒያኛው እርሳሶች ፊደሉ ተቀርጾ
ዜማው ተቀልጾ
የተሰናዳውን ትምህርት አመጡልን
እኛም ተማሪዎች እሺ መምህር አልን
እነሱ እኮ ማለት እረፍት የሚጾሙ
ስራን የሚያዜሙ
ለእኛው ተፈጥረው ለእኛው የሚኖሩ
መምህራን ናቸው በስራ የታሰሩ
ታድያ እነደነሱ ሀሳብ በነሱ ጎዳና
እኛን እየሳሉ
መማር መማር ብቻ!! መማር ብቻ ይላሉ
ምናልባት ምናልባት ማስተማሩ አምሮን
መምህሩ ደብሮን
ጥያቄ እንዳናጭር ሁሌም ሲያስተምሩን
መማር ነው ይሉናል የሚጠቅም ለሀገር
እኛም ተማሪዎች
ትእዛዝ ፈጣሚዎች
‘’በየኔታ ጉሮሮ ጠጅ ይንቆርቆር
በጠላት ጉሮሮ እንጨት ይሰንቀር’’
እንላለን እንማራለን
እኛ ሞተን ብናልፍ የልጅ ልጆቻችን በናንተ ይማሩ
እናንተኮ ማለት ለእኛ የምትኖሩ
ለሀገር የምትበሩ
ነዳችሁ ነዳችሁ መቼም የማታልቁ
እረፍት የማታውቁ
እንዲህ ናችውና እኛ ምንም አንል እርሱ ያሳርፋችሁ፡፡፡፡፡


05/08/05
.

No comments:

Post a Comment